Rollout Toolkit (Amharic)

ROBOCALL SCRIPT

የ[School name] የ8ተኛ ክፍል ቤተሰቦች: ተማሪዎ፣ በዲሲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያሏቸውን የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አማራጮቻቸውን እንዲዳስሱ ስለሚረዳቸው የመረጃ ምንጭ (resource) ወደእናንተ እየመጡላችሁ እንደሆነ – ለማሳወቅ እንወዳለን።  ወደ ‘ኮሌጅ እና የስራ-መስክ አካዳሚስ መምሪያው (The Guide to College and Career Academies)’፤ በልጅዎ የክልል ወሰን ውስጥ (in-boundary) በሚገኝ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና በDCPS ዙሪያ የሚገኙ ሌሎች ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ስለሚገኙ – የኮሌጅ እና የስራ-መስክ አዳካሚስ (Career Academies) የየግል መረጃዎችን የሚያጋራ ይሆናል።  የDCPS የኮሌጅ እና የስራ-መስክ አካዳሚ፤ የስራ-ልምምድን  እና ለኮሌጅ ዝግጁነትን የሚሰጥ፣ በዚያው በከፍተኛ-ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን – አነስተኛ የሆነ የመማሪያ ማህበረሰብ ነው። በDCPS የኮሌጅ እና የስራ-መስክ አካዳሚስ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች፤ ክፍያ የሚያገኙበት ኢንተርንሽፖች (internships)ን፣ የስራ-መስክ የመካሪነት አገልግሎት፣ እና ተማሪዎችን ከፍተኛ ደሞዝ ለማግኘት የበለጠ ተወዳዳሪ ወደሚያደርጋቸው – ከከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወይም ከኮሌጅ በኋላ ተፈላጊነት ወደአላቸው የስራ-መስኮች – በድርጅቶች-ዋጋ በሚሰጣቸው ሰርተፊኬቶች መመረቅ ይችላሉ።

ከኖቨምበር (November) 8 ሣምንት ጀምሮ፣ ወደ ‘ኮሌጅ እና የስራ-መስክ አካዳሚስ መምሪያው (The Guide to College and Career Academies)’ን፤ በፖስታ-ሣጥናችሁ ውስጥ መምጣቱን ተመልከቱ፤ ወይም ከአስፐን ፖርታል (Aspen portal) ላይ፣ ከዲሴምበር (December) መጀመሪያ ጀምሮ፣ ዳውንሎድ (download) አድርጉት።  ለጥያቄዎቻችሁ፣ የትምህርት ቤቱን ካውንስለር አነጋግሩ ወይም በdcpsguide@k12.dc.gov ኢሜል አድርጉ።

EMAIL TO FAMILIES

ጉዳዩ፡ ወደ ኮሌጅ እና የስራ-መስክ አካዳሚስ መምሪያ (Guide to College and Career Academies)፤ ለ8ተኛ ክፍል ተማሪዎች፣ ከኖቨምበር (Nov.) 8 ቀን ጀምሮ የሚገኝ ይሆናል።

ውድ የ[school name]  ቤተሰቦች:

በዲሲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሆናችሁ የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አማራጮቻችሁን የምትዳስሱበት የመረጃ ምንጭ (resource) ወደ እናንተ እየመጣ መሆኑን ሳጋራችሁ፣ ደስታ ይሰማኛል።  የወደ ኮሌጅ እና የስራ-መስክ አካዳሚስ መምሪያ (Guide to College and Career Academies)፤ ወደ DCPS ኮሌጅ እና የስራ-መስክ አካዳሚስ በየግል-የተዘጋጀ መምሪያ ሲሆን፣ ከእያንዳንዱ የ8ተኛ ክፍል ተማሪ ጋር እንዲጋራ የተደረገ ነው።

DCPS፣ ወደ ኮሌጅ እና የስራ-መስክ አካዳሚስ መምሪያ (Guide to College and Career Academies)ን ያዘጋጀው፤ ወደ የስራ-መስክ ጎዳናቸው እና ኮሌጅ፣ ተማሪዎቻቸውን ለማሰናዳት ምን ፕሮግራሞች እንደሚገኙ፣ ተጨማሪ መረጃዎችን መፈለጋቸውን አሳይተው – የተማሪ እና የቤተሰብን ባቀረቡት አስተያየት ላይ ምላሽ-ለመስጠት ነው። መምሪያው (The Guide)፤ ስለ ‘DCPS’ የኮሌጅ እና የስራ-መስክ አካዳሚስ (Career Academies)፤ በተማሪዎ በክልል-ወሰን ውስጥ ባለ የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና DCPS ዙሪያ በሚገኙ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ መረጃዎችን ያጋራል።

የDCPS የኮሌጅ እና የስራ-መስክ አካዳሚ፤ የስራ-ልምምድን  እና ለኮሌጅ ዝግጁነትን የሚሰጥ፣ በዚያው በከፍተኛ-ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኝ – አነስተኛ የሆነ የመማሪያ ማህበረሰብ ነው። በDCPS የኮሌጅ እና የስራ-መስክ አካዳሚስ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች፤ ክፍያ-የሚያገኙበት ኢንተርንሽፖች (internships)ን፣ የስራ-መስክ የመካሪነት አገልግሎት፣ እና ከከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወይም ከኮሌጅ በኋላ የስራ-መስክን ለመፈለግ ቀላል በሚያደርግላቸውን ሰርተፊኬቶች እንዲመረቁ ያደርጋቸዋል።

በDCPS ኮሌጅ እና የስራ-መስክ አካዳሚስ (College and Career Academies) ውስጥ የተመዘገቡ ተማሪዎች፤ ከከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመመረቁ ሁኔታዎች የሚታይባቸው፣ ኮሌጅ ገብተው የመማር ሁኔታ የሚታይባቸው፣ እና ከእነሱ ፍላጎቶች ጋር የሚጣጣሙ በርካታ ከሆኑ የስራ-ዕድሎች ጋር ወደሚያገናኛቸው የስራ-መስክ ጎዳና ወዲያውኑ ለመግባት የበለጠ ዕድሎች ይኖራቸዋል። የ8ተኛ ክፍል ተማሪዎች፣ በትክክል አሁን ምን ማድረግ እንዳለባቸው ላያውቁ ቢችሉም፤ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በኋላ ለሚገጥማቸው ሕይወት እንዲዘጋጁ የሚረዳቸውን ግሩም-የሆኑ ፕሮግራሞችን፤ ይህ ወደ ኮሌጅ እና የስራ-መስክ አካዳሚስ መምሪያው (Guide to College and Career Academies)ን፣ እንዲፈትሹ ይረዳቸዋል።

ወደ ኮሌጅ እና የስራ-መስክ አካዳሚስ መምሪያ (Guide to College and Career Academies)፤ በኖቨምበር (November) 8 ቀን በፖስታ-ሳጥናችሁ ውስጥ የምታገኙበትን፤ እና በአስፐን (Aspen) የወላጅ ፖርታል  ላይ ደግሞ፣ በዲሴምበር (December) 2021 መጀመሪያ ላይ ጀምሮ ይገኛል። መመሪያው (The Guide)፣ በ“Documents” በሚለው መስመር (tab) ላይ የሚገኝ ይሆናል።

ስለ መምሪያው (Guide) ወይም የDCPS ኮሌጅ እና የስራ-መስክ አካዳሚዎች (Career Academies)፤ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፤ ወደ bit.ly/dcpsmsguide ሂዱ። ሁሉንም የDCPS የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አማራጮችን – ይህም፤ የኮሌጅ እና የስራ-መስክ አካዳሚን የማያንፀባርቁትን፣ ነገር ግን ሌላ ትኩረት ያላቸውን ያከተተን – በDCPS የምዝገባ ድህረ-ገጽ ላይ በenrolldcps.dc.gov መፈተሽ ትችላላችሁ።

ስለ ወደ ኮሌጅ እና የስራ-መስክ አካዳሚስ መምሪያ (Guide to College and Career Academies) ለሚኖሩ ጥያቄዎች፤ የትምህርት ቤት ካውንስለርን ያነጋግሩ ወይም በdcpsguide@k12.dc.gov ኢሜል አድርጉ። ተማሪዎን፣ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ኮሌጅ፣ እና የስራ-መስኮች በሚያደርጉት ጉዞ ስንረዳቸው ደስታ ይሰማናል።

ከሰላምታ ጋር፣

[name]