የኮሌጅ እና ሙያ አካዳሚ (College and Career Academies) መምሪያ: ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦች በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

የኮሌጅ እና የትምህርት አካዳሚ (College and Career Academy) ምንድነው? በኮሌጅ እና ሙያ አካዳሚ መመዝገብ የሚያስገኘው ጥቅም ምንድነው?

የዲሲፒኤስ ኮሌጅ እና ሙያ አካዳሚ (DCPS College and Career Academy) በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ የሙያ ስልጠና እና የኮሌጅ ዝግጁነትን የሚሰጥ አነስተኛ የመማሪያ ማህበረሰብ ነው። በዲሲፒኤስ ኮሌጅ እና ሙያ አካዳሚዎች (DCPS College and Career Academies) ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ደሞዝ የሚከፈልባቸው የስራ ልምምዶች ( paid internships)፤ የሙያ ማለማመድ (career mentoring)፤ እድሎች የሚኖራቸው ሲሆን ከሁለተኛ ደረጃ ወይም ከኮሌጅ በኋላ ስራ ለማግኘት ቀላል በሚያደርግላቸው የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት(certifications) ሊመረቁ ይችላሉ።

በዲሲፒኤስ የኮሌጅ እና ሙያ አካዳሚዎች የተመዘገቡ ተማሪዎች (DCPS College and Career Academies)  በአብዛኛው ሁለተኛ ደረጃን ያጠናቅቃሉ፤ በአብዛኛው ኮሌጅ ይገባሉ፤ እንዲሁም ለፍላጎታቸው ተመጣጣኝ ወደሆነ የስራ መንገድ በፍጥነት የመግባት እድሎች ይኖራቸዋል። የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች አሁን በትክክል ምን ማድረግ እንደሚኖርባቸው ላያውቁ ስለሚችሉ የኮሌጅ እና ሙያ አካዳሚዎች (College and Career Academies) መምሪያ  በዲሲፒኤስ የሚገኙ እና ከሁለተኛ ደረጃ በሁዋላ ላለ ህይወታቸው የሚያዘጋጇችወን በጣም ጠቃሚ መርሃ ግብሮች እንዲመረምሩ ይረዳቸዋል።

በመመሪያዬ ላይ የተካተተው የሙያ ክላስተር (Career Cluster) መረጃ ከየት መጣ?

በፀደይ (spring) 2020 አንዳንድ የ 7 ኛ ክፍል ተማሪዎች በርቀት ትምህርት ከመጀመራቸው በፊት በትምህርት ቤታቸው ውስጥ የሙያ ክላስተር ዳሰሳ ጥናት (Career Cluster Survey) የመሳተፍ ዕድል ነበራቸው። እነዚያ ተማሪዎች ከላይ የተዘረዘሩትን የግል የሙያ ጥናት መረጃዎችን ወደ ኮሌጅ እና የሙያ አካዳሚዎች (College and Career Academies) መመሪያዎችን ተቀብለዋል።

ባለፈው የፀደይ ወቅት የሙያ ክላስተር ዳሰሳ ጥናት የመውሰድ ዕድል ከሌለዎት እና አሁን ከሙያ ፍላጎቶችዎ ጋር ሊጣጣሙ ስለሚችሉ አስደሳች የሙያ መንገዶች የበለጠ ለመመርመር ከፈለጉ፤ የዳሰሳ ጥናቱን በ ናቪያንስ (Naviance) ያገኛሉ። ለናቪያን እንዴት መመዝገብ እንደሚችሉ ያሚያሳየውን መረጃ እዚህ ያግኙ እና ጥናቱን ይውሰዱ!

“በክልል ውስጥ” (“in-boundary”) ትምህርት ቤት ምንድነው?

የክርስዎ የክልል (in-boundary) ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በቤተሰብዎ የቤት አድራሻ መሠረት የመከታተል መብት ያለዎት የዲሲፒኤስ (DCPS) ትምህርት ቤት ነው። በዲሲ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ተማሪ ከመዋዕለ-ሕጻናት እስከ 12ኛ ክፍሎችን በክልሉ (in-boundary) ትምህርት ቤት የመከታተል መብት አለው። የተማሪውን የክልል (in-boundary) ት/ቤት ለመለየት ወደ enrolldcps.dc.gov/node/41 ይሂዱ።

ተማሪዎች በመጋቢ አደረጃጀት (feeder pattern) ትምህርት ቤታቸው የመከታተል ችሎታ ሊኖራቸው ይችላል።  መጋቢ ትምህርት ቤት (feeder pattern school) የአሁኑን ትምህርት ቤትዎ የተርሚናል (terminal) ክፍል ማጠናቀቅን መሠረት በማድረግ የመከታተል መብት ያለዎት ትምህርት ቤት ነው።  

ከክልልዎ (in-boundary) ወይም መጋቢ (feeder pattern) ውጪ የሚገኝ ማንኛውም ት/ቤት ለመግባት በ ማይ ስኩል ዲሲ ሎተሪ (My School DC lottery) ሂደት፤ ማለትም በዚህ ዓመት ዲሴምበር 14 ተከፍቶ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ላሉ ክፍሎች በፌብሩዋሪ 1 2021 የሚዘጋው፤ ሂደት መሰረት ቤተሰብዎ ማመልከቻ መሙላት አለበት። አንዳንድ የዲሲፒኤስ (DCPS) ትምህርት ቤቶች የተለየ የመቀበያ መስፈርቶች አሏቸው — በዚህ መምሪያ የተካተቱትን ሶስት ት/ቤቶች ጨምሮ፤ ማክኪንለይ የቴክኖሎጂ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (McKinley Technology High School)፤ ፐልፕስ ስነ-ህንጻ፤ ግንባታ እና ምህንድስና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (Phelps Architecture, Construction and Engineering High School) እና ኮሎምቢያ ሃይትስ የትምህርት ካምፓስ (Columbia Heights Education Campus (CHEC))።

ስለ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አማራጮች እና መጋቢዎች የበለጠ ለመረዳት enrolldcps.dc.gov ይጎብኙ።

ቤተሰቦቼ ወደሌላ ቦታ ተዛወሩ፤ እናም አሁን የተለየ የክልል “in-boundary” ሁለተኛ ደረጃ ነው ያለኝ። አዲሱ የክልል “in-boundary” ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ምን ምን እንደሚሰጥ መረጃ ከየት ላገኝ እችላለሁ?

ቤተሰቦችዎ ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ ተዛውረው ከሆነ ፣ የ ኮሌጅ እና የሙያ አካዳሚዎች (College and Career Academies) መመሪያ ከሚያሳየው የተለየ የክልል “in-boundary” ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሊኖርዎት ይችላል። ከመምሪያው በስተጀርባ የሚገኘውን የተለያዩ የኮሌጅ እና የሙያ አካዳሚዎች (College and Career Academies) አማራጮች ይመልከቱ። ስለ ዲሲፒኤስ የኮሌጅ እና የሙያ አካዳሚዎች (DCPS College and Career Academies) የበለጠ ለመመርመር  dcpscte.org ን መመልከትም ይችላሉ።

አንዳንድ የዲሲፒኤስ (DCPS) የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በመምሪያው ላይ የሉም — ይህ ለምንድነው?

የኮሌጅ እና የሙያ አካዳሚዎች መመሪያ (College and Career Academies) ከህዝብ ደህንነት እና አመራር እስከ ምህንድስና እስከ መስተንግዶ እና የምግብ አሰራር ስራዎች ድረስ በተለያዩ የሙያ ጎዳናዎች ላይ ዕድሎችን የሚሰጡ አነስተኛ የመማሪያ ማህበረሰብ የሆኑ የኮሌጅ እና የሙያ አካዳሚዎች ያላቸውን የዲሲፒኤስ (DCPS) ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶችን ያሳያል። በአጠቃላይ አስራ ሁለት የዲሲፒኤስ (DCPS) ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የኮሌጅ እና የሙያ አካዳሚዎችን ያቀርባሉ። ኮሌጅ እና የሙያ አካዳሚዎችን በማይሰጡ በሌሎች የዲሲፒኤስ (DCPS) ሁለተኛ ደረጃ ት / ቤቶች ለኮሌጅ እና ለሙያ ዝግጅት ሌሎች ታላላቅ አማራጮች አሉ – ለምሳሌ በዱክ ኤሊንግተን ሥነ-ጥበባት ትምህርት ቤት (Duke Ellington School for the Arts) ወይም በዓለም አቀፍ የባካላሬት ፕሮግራም በቤንጃሚን ባንኔከር ከፍተኛ ትምህርት ቤት (International Baccalaureate program at Benjamin Banneker High School). ለእርስዎ በጣም ተስማሚ የሆነውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አማራጭን በሚመርጡበት ጊዜ፤ ዲሲፒኤስ (DCPS) የሚያቀርባቸውን በርካታ አማራጮች እንዲመለከቱ  እናበረታታዎታለን።

በክልል (in-boundary) የሁለተኛ ደረጃ ት / ቤቴ ስለሚገኙ የምስክር ወረቀቶች እና የሥራ ልምምድ እድሎች የበለጠ መስማት እፈልጋለሁ ፡፡ ተጨማሪ የት ማግኘት እችላለሁ?

እያንዳንዱ ኮሌጅ እና የሙያ አካዳሚ (College and Career Academy) በተከፈላቸው የሥራ ልምምዶች አማካይነት በትምህርት ትኩረታቸው ውስጥ በሙያ ጎዳናቸው ላይ እውነተኛ የሕይወት ተሞክሮ እድሎችን ለተማሪዎች ሰጣል። ለምሳሌ በዉድሮው ዊልሶን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በሚገኘው አካዳሚ ኦፍ ሆስፒታሊቲ (Academy of Hospitality at Woodrow Wilson High School)፤ ኮሎምቢያ ሃይይስ ኢዱኬሽን ካምፓስ (Columbia Heights Education Campus) ወይም ባሉ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (Ballou High School) የተመዘገቡ ተማሪዎች በእንግዳ ተቀባይነት ኢንዱስትሪ ውስጥ የመስራት ተሞክሮ እንዲያገኙ በቀጠናው በሚገኝ ሆቴል የስራ ላይ ልምምድ ለማግኘት ይችላሉ፡፡  

የአካዳሚ ተማሪዎችም ለስራ መጀመር የሚያስችላቸውን ኢንዱስትሪ-ተኮር የምስክር ወረቀቶችን ለመውሰድ ይዘጋጃሉ፡፡ ለምሳሌ የምግብ አሰራር ተማሪዎች የሰርቭሴፍ (ServSafe) የምስክር ወረቀት ያጠናቅቃሉ፤ የዲጂታል ሚዲያ እና ማስ ሚዲያ ተማሪዎች  (Digital Media and Mass Media) የአዶቤ ፕሪፒየር ፕሮ እና ፖቲሾፕ (Adobe Premier Pro and Photoshop) የምስክር ወረቀት ያጠናቅቃልይ፤ እንዲሁም የ አይቲ (IT) ተማሪዎች የኮምፕቲያ ኤ + እና ኮምፕቲያ ኤ + ሴኩሪቲ (CompTIA A+ and CompTIA A+ Security) የምስክር ወረቀት ያጠናቅቃሉ፡፡

በርስዎ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አካዳሚዎች ውስጥ ስለ የስራ ተለማማጅነት (internship) ዕድሎች እና የምስክር ወረቀቶች ለማወቅ እባክዎ dcpscte.org ን ይጎብኙ፡፡ እንዲሁም ለዲሲፒኤስ (DCPS) ተማሪዎች የስራ ተለማማጅነት (internship) ዕድሎች በ dcpsinternships.org የበለጠ መመርመር ይችላሉ፡፡

በአስፐን (Aspen) ውስጥ ለኮሌጅ እና ሙያ አካዳሚዎች መመሪያዬን እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

ዲሲፒኤስ (DCPS) የሁሉንም የ 8 ኛ ክፍል ተማሪዎች ለኮሌጅ እና ለሙያ የሥራ አካዳሚዎች የመመሪያ (Guide to College and Career Academies) ቅጅ በፖስታ ወደ ቤታቸው ልኳል ፣ ነገር ግን ቤተሰቦች የመመሪያውን ቅጅ በአስፐን ፓረንት ፖርታላችው (Aspen Parent Portal) ማግኘት ይችላሉ፡፡ አስፐን (Aspen) ከገቡ በኋላ፤ ፐብሊሸር ረፖርትስ (“Published Reports) በሚለው ስር የኮምፕዊተርዎ ስክሪን የታችኛው ቀኝ ክፍል በመሄድ ለኮሌጅ እና ለሙያ የሥራ አካዳሚዎች የመመሪያ (Guide to College and Career Academies)ን ማግኘት ይችላሉ፡፡ ወይም ደግሞ ፋሚሊ (“Family”) የሚለውን በመጫን በላይኛው የኮምፒውተርዎ ስክሪን ዶክመንትስ (Documents) የሚለው ክፍል ያገኙታል፡፡ ለበለጠ ዝርዝር መረጃ bit.ly/dcpsmsguide ን ይጎብኙ፡፡

ወደ አስፐን ፓረንት ፖርታል (Aspen Parent Portal) ለመግባት እርዳታ ከፈለጉ, በዲሲፒኤስ ድረ ገጽ ላይ አስፐንን (Aspen) በሚመለከት ማብራሪያ ያግኙ ፡፡ 

ቀጣይ እርምጃዎቼ ምን መሆን አለባቸው?

ስለ የተለያዩ የዲሲፒኤስ የሁለተኛ ደረጃ ት / ቤት አማራጮች የበለጠ ለመመርመር የኮሌጅ እና ሙያ አካዳሚዎች መመሪያን (Guide to College and Career Academies) ይጠቀሙ። ከክልልዎ (in-boundary) የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትዎ ፣ ከኮሌጁ እና ከሙያ አካዳሚዎችዎ እእንዲሁም ከሌሎች የዲሲፒኤስ (DCPS) የሁለተኛ ደረጃ ት / ቤት ምርጫዎች ጋር ለመገናኘት ብዙ እድሎች አሉ።

  • ኢዲኤፍኢኤስቲ (EdFEST)፤ የዲስትሪክቱ አመታዊ የህዝብ ት/ቤቶች በአል፤ በዚህ አመት በርቀት ዲሴምበር 12፣ 2020 ይካሄዳል፡፡ በ www.myschooldc.org ላይ የበለጠ መረጃ ያግኙ፡፡
  •  Learn about ስለ የዲሲፒኤስ ት/ቤት ኦፕን ሃውስ (DCPS school open houses) በዲሲፒኤስ መመዝገቢያ ድረ ገጽ  (DCPS Enrollment website) ላይ መረጃ ያግኙ፡፡
  •  ማይ ስኩል ዲሲ ሎተሪ (My School DC lottery) ዲሴምበር 14፤ 2020 ይከፈታል፡፡ የማይ ስኩል ዲሲ ድረ ገጽን፡ www.myschooldc.org ይጎብኙ፡፡